የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊ እና የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሩ እና ረዳት ዋና ፀሀፊው የመንግስታቱ ድርጅት ለሀገራዊ ልማት ዕቅዶች የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያሳድግ በሚያስችሉ ማሻሻያዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን አጋርነት እና ትብብር የበለጠ በማጠናከር ሀገራዊ የልማት ጥረቶችን መደገፍ እና ለሰብአዊ ሁኔታዎች ምላሽ መስጠት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ገንቢ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ሀገራዊ የትኩረት መስኮችን እና ትልሞችን እውን ለማድረግ ቅንጅትን እና ውጤታማነትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር ታዬ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወሳኝ የልማት አጋር እንዲሆን እና ለአባል ሀገራቱ ውጤታማ ድጋፍ ማድረግ እንዲችል የተቋሙን አሰራሮችና ትኩረቶች ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም ዶ/ር ራሚዝ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው አረጋግጠውላቸዋል።
ዶ/ር ራሚዝ በበኩላቸው ÷ጽ/ቤታቸው የኢትዮጵያን የልማት እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።