July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ግጭቶችና ጦርነቶች በአለም አቀፍ ደረጃ አዳዲስ በሽታዎች እንዲከሰቱ ምክንያት መሆናቸውን የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ።

ዋና ጸሀፊው በ2024 ብቻ በደንጌ፣ ኮሌራና ሌሎች በሽታዎች ተይዘው ክትባት የሚሹ 20 ሚሊየን ህጻናት መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል።በጋዛ እና ሱዳን ሚሊየኖች በጥይት ብቻ ሳይሆን መታከም ባልቻሉ በሽታዎችና በምግብ እጥረት ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚገኝም ነው ያነሱት።በጤና ተቋማት ላይ የሚደረሰው ጉዳት መጠን በሀላፊነት ዘመኔ አይቸው የማላውቀው ነው ያሉት የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ የፊታችን ሀሙስ የሚጀመረው የአለም ጤና ጉባኤ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስበዋል።

Al-Ain