January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ በዓለም የጤና ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

77ኛው የዓለም ጤና ጉባዔ በስዊዘርላንድ ጀኔቫ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል፡፡“ሁሉም ለጤና፣ ጤና ለሁሉም” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ ላይ ከ190 በላይ አባል ሀገራት ተወካዮችና ሌሎች አካላት ተሳትፈዋል፡፡በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክም በጉባዔው ላይ እየተሳተፈ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡በተለያዩ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳዎች ላይ የሚመክረው ጉባዔው እስከ ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡

FBC