ግዙፉ የአውሮፕላን አማራች ኩባንያ ቦይንግ፤ የአፍሪካ ዋና መቀመጫውን በኢትዮጵያ ሊከፍት መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ የኩባንያው ውሳኔ ተቋሙ ዋና መቀመጫውን በኬኒያ አሊያም በደቡብ አፍሪካ ሊያደርግ እንደሚችል ሲሰጡ የነበሩ ግምቶችን ያስቀረ እና ኢትዮጵያ ቀዳሚ ምርጫው መሆኗን ያረጋገጠ ነው፡፡ እ.አ.አ በ2023 ኢትዮጵያ እና ቦይንግ ኩባንያ የተወሰኑ የአውሮፕላን ክፍሎችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማምረት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡ የአፍሪካ አየር መንገዶች በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ1 ሺህ በላይ አዳዲስ አውሮፕላኖችን እንደሚፈልጉ የኩባንያው ጥናት ያመላክታል፡፡ ከእነዚህ ወስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት አዳዲስ አውሮፕላኖች የአየር መንገዶቹን መዳረሻ ለማስፋት እንደሚያገለግሉ ዲደብሊው አፍሪካ ዘግቧል፡፡
EBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።