የኢትዮ-ፓኪስታን የኢኮኖሚ ትብብር ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በፎረሙ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ከ80 በላይ የፓኪስታን ባለሃብቶች ተሳትፈዋል፡፡
በተጨማሪም የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሃና አርአያ ስላሴ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና ሌሎች የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ፎረሙ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ያጠናክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።