January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የምክክር ምዕራፍን በመዲናዋ ሊጀምር ነው

 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የከተማ አስተዳደር (ክልላዊ) የምክክር ምዕራፉን በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚጀምር አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፤ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በሚጀምረው በዚህ ምዕራፍ ላይ የሚከናወኑ ሦስት ዋና ዋና ተግባራትን ይፋ አድርጓል።

በቀዳሚነት ለምክክሩ የሚቀርቡ ተሳታፊዎች በምክክርና በውይይት የአጀንዳ ሀሳቦችን እንደሚያመጡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሂሩት ወልደስላሴ ተናግረዋል።

እነዚሁ ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎቻቸውን የጋራ በማድረግ አሰባስበውና አደራጅተው የመፍትሔ ሀሳቦችን ያቀርባሉ ተብሏል።

በመጨረሻም የሂደቱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊ የሚሆኑ ተወካዮቻቸውን እንደሚመርጡም ነው የተገለጸው።

በአዲስ አበባ ከተማ የተለዩ 2 ሺህ 500 የሚሆኑ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፉበትን ይህ የምክክር ምዕራፍ ለሠባት ቀናት የሚቆይ ነው።

FBC