January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የሥራ ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢ ተፈራርመውታል።

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሠለሞን ሶካ እና ዳንኤ ተሬሳ፣ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሁመድ፣ በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢ ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ስምምነቱ ወደኩዌት የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ኢትዮጵያዊያን መብትና ጥቅማቸው ተጠብቆ ህጋዊ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን የትብብር ሁኔታ ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።

FBC