July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአሜሪካ ኤርፖርቶች በአንድ ቀን ብቻ ሶስት ሚሊዮን መንገደኞችን አስተናገዱ

ያሳለፍነው አርብ ዕለት በታሪክ ብዙ መንገደኞች የተስተናገዱበት ዕለት ሆኖ ተመዝግቧል

የአሜሪካ አቪዬሽን ባለስልጣን በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ 271 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል

የአሜሪካ ኤርፖርቶች በአንድ ቀን ብቻ ሶስት ሚሊዮን መንገደኞችን አስተናገዱ፡፡

በአሜሪካ የክረምት ወራት የሚጀመርበት ወቅት መድረሱን ተከትሎ አየር መንገዶች በመንገደኞች ብዛት እየተጥለቀለቁ ይገኛሉ፡፡

ያሳለፍነው አርብ ዕለትም ብቻ የአሜሪካ ኤርፖርቶች 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን መንገደኞችን እንዳስተናገዱ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

እንደ ኒዮርክ አይነት ብዙ በረራ የሚደረግባቸው ከተሞች በአየር ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች እጥረት ምክንያት በረራዎችን ሰርዘዋል ተብሏል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ በአንድ ቀን በረራ ያደረጉ መንገደኞች ቁጥር በታሪክ ከፍተኛው ዕለት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን የመንገደኞች ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ ይጠበቃልም ተብሏል፡፡