July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ ለመገንባት ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ

ሞስኮ የነዳጅ ማደያውን ለመገንባት ያሰበችው በሱዳን ነው ተብሏል

የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ለሩሲያ ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ መስጠቱ ተገልጿል

ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ ለመገንባት ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ፡፡

በእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለችው ጎረቤት ሀገር ሱዳን ሩሲያ በቀይ ባህር የነዳጅ ማደያ እንትገነባ ጥያቄ እንደቀረበላት አስታውቃለች፡፡

በሱዳን ጦር ውስጥ አመራር የሆኑት ጀነራል ሰር አል አታ እንዳሉት ሱዳን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማግኘት በሚል ከሩሲያ የቀረበላትን ጥያቄ እንደምትቀበል ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ይህን ስምምነት በቀርቡ ሊፈራረሙ እንደሚችሉ አል አረቢያ ጀነራል ያሰር አል አታን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

ሩሲያ እስካሁን በሱዳን ጦር አመራር ይፋ ስለተደረገው የቀይ ባህር ነዳጅ ማደያ ግንባታ ዙሪያ በይፋ ያለችው ነገር የለም፡፡

ሩሲያ በቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር አስተዳድር ጊዜ በፖርት ሱዳን ወታደራዊ ማዘዣ ለመገንባት ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር፡፡

ፕሬዝዳንቱ በመፈንቅለ ስልጣን ከተወገዱ በኋላ ይህ ስምምነት ሳይተገበር እስካሁን የቆየ ሲሆን የሱዳን ወታደራዊ መንግስት ስምምነቱን እየገመገመ መሆኑን በተደጋጋሚ አስታውቋል፡፡

Al-Ain