January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የወጣቶች ድምጽ ለሀገራዊ ምክክር የግንዛቤ ማስጨበጫ የማህበራዊ ድህረ ገጽ ንቅናቄ ይፋ ተደረገ

በሀገራዊ ምክክሩ የወጣቶችን ሁሉ አቀፍ ተሳትፎ ለማጠናከር የሚያስችል የማህበራዊ ድህረ ገጾች የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ ይፋ ተደርጓል፡፡

የወጣቶች ድምጽ ለሀገራዊ ምክክር በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው ንቅናቄ ወጣቶች በሀገራዊ ምክክሩ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ረገድ የመሪነት ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል።

በንቅናቄው ከተለያዩ ማህበራት የተወጣጡ ወጣቶች፣ በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎች፣ በሚዲያና ፈጠራ ስራ የተሰማሩ ወጣቶችን እንደሚያሳትፍ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መረጃ አመልክቷል።

የንቅናቄ መድረኩ ለሶስት ወር የሚዘልቅ ሲሆን ወጣቶችን ተደራሽ ለማድረግ የታለመ መሆኑም ተነግሯል።

FBC