July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፕሬዝዳንት ፑቲን በሞስኮ ያለው የአሜሪካን ኤክስፕረስ ቢዝነስ እንዲዘጋ አዘዙ

አሜሪካን ኤክስፕረስ የተሰኘው የንግድ ተቋም በሩሲያ ያለው ንግድ እንዲዘጋ ተወስኗልቀዳሚ ገፅዜናአስተያየትፖለቲካኢኮኖሚማህበራዊልዩልዩስፖርትየመረጃ ሳጥንተመልከትፖለቲካፕሬዝዳንት ፑቲን በሞስኮ ያለው የአሜሪካን ኤክስፕረስ ቢዝነስ እንዲዘጋ አዘዙአሜሪካን ኤክስፕረስ የተሰኘው የንግድ ተቋም በሩሲያ ያለው ንግድ እንዲዘጋ ተወስኗልአል-ዐይን 2024/5/24 7:43 GMTየአውሮፓ ህብረት 223 ቢሊዮን ዶላር የሩሲያን ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ ማገዱ ይታወሳልፕሬዝዳንት ፑቲን በሞስኮ ያለው የአሜሪካን ኤክስፕረስ ቢዝነስ እንዲዘጋ አዘዙ፡፡ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን መላኳን ተከትሎ በአውሮፓ እየተካሄደ ያለው ያለው ጦርነት ከተጀመረ ሶስተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ይህ ጦርነት በሩሲያ ላይ ከስድስት ሺህ በላይ ማዕቀቦች እንዲጣሉባት ከማድረጉ ባለፈ ለዓለም ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ መናርም ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡አሜሪካ እና ምዕራባዊያን ሀገራት ከማዕቀቡ ባለፈ የሩሲያ መንግስት እና ባለሀብቶች ንብረት የሖኑ ሁሉንም ሀብቶች እንዳይንቀሳቀሱ ያገዱ ሲሆን ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት የሩሲያዊያንን ገንዘብ ማዋል ጀምረዋል፡፡በተለይም የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ የታገዱ የሩሲያዊያን መንግስት እና ዜጎች ሀብትን ለዩክሬን መልሶ ግንባታ እንዲውል በመወሰን ላይ ይገኛሉ፡፡የአውሮፓ ህብረት ባሳለፍነው ሳምንት እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ የሩሲያ ገንዘብ ውስጥ ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለዩክሬን እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል፡፡ሩሲያ ለህብረቱ ውሳኔ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ በወቅቱ ገልጻ የነበረ ቢሆንም በሀገሯ ያሉ የምዕራባዊያን ሀገራትን ሀብት ማገድ ጀምራለች፡፡

Al-Ain