ሀገራዊ ምክክር” የሚለውን ሀሳብ “በጎ ነገር ሁሉ መልካም ነው” በሚለው ብሂል መሰረት መቀበል ተገቢ ከመሆኑ በተጨማሪ፤”ምክክር” የሚለው ቃል ቁርዓናዊ መሰረት ያለው መሆኑን ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ገለጹ።የእስልምና ሐይማኖት መምህሩ ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ ከኢቢሲ ሳይበር ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ሀገራዊ ምክክር ምርጫ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን በመጥቀስ፤”አላህ በመካከላችሁ ምክክር ይኑር” ሲል የደነገገው ትዕዛዝ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ነው ያሉት።“በመካከላችሁ ምክክር ይኑር” የሚለው የቁርዓን አንቀፅ ቤተሰብን ብቻ ሳይሆን ሀገርን ጭምር የሚመለከት ነው ብለዋል።“የእስልምና እምነት ለሰላም የሚሰጠው ዋጋ በጣም ትልቅ ነው፤ ከጌታችን አላህ ምርጥ ስሞች መካከል አንዱ ‘አሰላም’ (ሰላም) የሚለው ነው” ሲሉ አመላክተዋል።”በየዕለቱ 5 ጊዜ ሰላት ሰግደን (ጸሎት አድርገን) ስናበቃ የምንደመድመው ‘አላህ ሆይ፥ አንተ ሰላም ነህ፤ ሰላም የሚመነጨው ከአንተ ነው’ በማለት ነው፤ ይህ ደግሞ እስልምና ለሰላም ያለውን ትልቅ ቦታ ያሳያል” ነው ያሉት።ሀገራዊ ምክክሩ አንዱ ተሸናፊ፣ አንዱ አሸናፊ በማይሆንበት መንገድ የሚካሄድ በመሆኑ፤ እንደ እስልምና አስተምህሮ የተበደለ ሰው ይቅርታ ቢያደርግ ትልቅ ይባላል እንጂ አያንስም ብለዋል።
EBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።