January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ለማሳካት የግሉ ዘርፍ የመሪነት ሚና መወጣት እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሚኒስትሮች እና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ባለድርሻዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ዲጂታላይዜሽን አይቀሬ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ወሳኝ ኢኒሼቲቮችን ቀርፃ መተግበር ጀምራለች ብለዋል።ለኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንን ማፋጠን የግድ የሆነባቸው ምክንያቶች አሉ ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አንደኛው፥ ዲጂታላይዜሽን ዕድገትን የሚያፋጥን በመሆኑ ነው ብለዋል። ሁለተኛው፥ መንግሥታዊ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እንደሚያግዝ ታምኖ መሆኑን ገልፀዋል።

EBC