ከችግሮች ነፃ የሆነች ኢትዮጵያን እውን ሆና ለማየት ምክክሩ ሊያመልጠን አይገባም ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰላምና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ ገለጹ።የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን “የኢትዮጵያ ሚዲያ ለኢትዮጵያውያን ውጤታማ ሀገራዊ ምክክር” በሚል መሪ ሃሳብ ከፌዴራል፣ ከክልል፣ ከግል የሚዲያ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ነው።አቶ እውነቱ፤ የምክክር ኮሚሽኑን በተመለከተ ከገለልተኝነት ጋር ተያይዞ የሚቀርብበት ወቀሳ በሕግ የተፈታ ነው ሲሉም ተናግረዋል።ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ ቢሆንም፤ ምክር ቤቱ ስራውን ከማገዝ ያለፈ ጣልቃ አይገባበትም ነው ያሉት።መገናኛ ብዙኀንም የተሳካ ምክክር እንዲደረግና ልዩነቶች በሰለጠነ መንገድ እንዲፈቱ አቅም ሊሆኑ እንደሚገባም ገልጸዋል።
EBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ