ዘላቂ እና አዎንታዊ ሰላምን ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ የተለያዩ አጋር አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም የተመራ ልዑክ በሰሜን አሜሪካ ዩታሃ ግዛት ከሚገኘው የስተርሊንግ ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር በሰላም ግንባታ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።
አቶ ብናልፍ አንዷለም በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በግዛቲቱ በወጣቱና አዛውንቶች እየተሰጠ ያለው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በአካባቢው ሰላም ለማምጣትና ጠንካራ ግዛት ለመፍጠር ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከዚህ ተግባር እንደ ሀገር ብዙ እንደምትማር ነው ሚኒስትሩ ያስገነዘቡት፡፡
የስተርሊንግ ፋውንዴሸን በኢትዮጵያ ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
የፋውንዴሽኑ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ኒኮል እስተርሊንግ በበኩላቸው÷ መንግስት ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፋውንዴሽኑ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት በግዛቷ የሰብዓዊ መስጫ ማዕከላትን፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች በመከባበርና በሰላም አብረው በአካባቢው ሰላም፣ አብሮነትና መከባበር ለማምጣት የሚያከናውኑ ተግባራትንና የተገኘውን ውጤት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በተጨማሪም በግዛቲቱ ከሚገኙ በሰላም ግንባታ ዙሪያ ከሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት አመራሮች ጋር መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።