July 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በኢትዮጵያና ሳዑዲ የሥራ ስምሪት ላይ የሚስተዋሉ የአሰራር ውስንነቶች ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ተባለ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከሳዑዲ ዓረቢያ የሰው ሃብትና ማህበራዊ ልማት ሚኒስቴር ዴዔታ አብዲልዋሃብ አልአጌል ጋር በሪያድ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ በዜጎች ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ዙሪያ የሁለትዮሽ ምክክር ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወ/ሮ ሙፈሪያት÷ በሀገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ማጠናከር በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ትኩረት እንደተሰጠው አንስተዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት የተጀመረው አዲስ የሥራ ስምሪት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡንም አብራርተዋል።

ቀጣይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ቴክኒካል ቡድን አዋቅሮ በሥራ ሂደቱ ላይ የሚገጥሙ ችግሮችና እድገቶችን እየተወያዩ ለመፍታት ሂደቱን የተሻለ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

አብዲልዋሃብ አልአጌል በበኩላቸው÷ በአዲሱ የሥራ ስምሪት ኢትዮጵያዊያን ተፈላጊነታቸው እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፤ አሁን የሚታዩ የአሰራር ውስንነቶች በመቅረፍ ለዘርፉ ውጤታማነት በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች በሳዑዲ ካላቸዉ ተፈላጊነት አንጻር ሰራተኞችን በማሰልጠን የሥራ ስምሪቱን የተደራጀ ለማድረግ መንግስታቸው እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

FBC