January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 1 ሺህ 445ኛውን የሐጅ ጉዞ በስኬት ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቀቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 1 ሺህ 445ኛውን የሐጅ ጉዞ በስኬት ለማካሄድ የሚያስችለውን ልዩ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ይህ ልዩ ዝግጅት ለተከታታይ ዓመታት የተደረገ መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ማለትም ጂዳ፣ መዲና፣ ሪያድ እና ደማም ከተሞች በሣምንት 35 የመንገደኛ በረራ እያደረገ እንደሚገኝም ነው ያስታወቀው፡፡በተጨማሪም ሥድስት የጭነት በረራ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡

FBC