January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢራኑን ፕሬዚዳንት ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለስልጣናትን አሳፍሯል” የተባለ ሄሊኮፕተር መከስከሱ ተነገረ

የኢራኑን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይስን ጨምሮ ከፍተኛ የሀገሪቱን ባለስልጣናት አሳፍሯል” የተባለ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር በምሥራቅ አዘርባጃን መከስከሱን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡እንደ ቴህራን ታይምስ ዘገባ በበረራ ላይ የነበሩት ሦስት ሄሊኮፕተሮች ሲሆኑ ሁለቱ በመዳረሻቸው አርፈዋል፡፡በሌላ በኩል “በተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ውስጥ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲን ጨምሮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አሚር አብዶላህያን፣ የአያቶላህ አል ሀሺም መስጂድ ኢማም እና የምሥራቅ አዘርባጃን ግዛት አሥተዳዳሪ ማሌክ ራህማቲ ሳይሳፈሩ እንዳልቀሩ” ግምታዊ ዘገባዎች እየወጡ ነው፡፡ይሁን እንጂ በተከሰከሰው ሄሊኮፕተር ውስጥ በትክክል እነማን ተሳፍረው እንደነበር ጥርት ያለ መረጃ አለመኖሩ የተመላከተ ሲሆን÷ የሄሌኮፕተሩ አደጋ መንስኤ ምን እንደሆነም ማብራሪያ አለመኖሩን ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘግቧል፡፡ፕሬዚዳንት ራይሲ ዛሬ በምሥራቃዊ አዘርባጃን ግዛት ተገኝተው የቂዝ ቃላሲ ግድብን መርቀው በመመለስ ላይ ሳሉ የተሳፈሩበት ሄሊኮፕተር ሳይከሰከስ እንዳልቀረ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡

FBC