በጃፓን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ፓራ-አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡በሻምፒዮናው በአራት የጉዳት ዘርፎች ከተሳተፉ አትሌቶች መካከል ትዕግስት ገዛኸኝ በ1 ሺህ 500 ሜትር (ቲ13 ቡድን) በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች፡፡አትሌት ትዕግስት ርቀቱን ያጠናቀቀችበት 4 ደቂቃ 18 ሰከንድ 90 ማይክሮ ሰከንድ የዓለም ሪከርድ ሆኖ መመዝገቡም ተመላክቷል፡በሌላ በኩል አትሌት ያየሽ ጌጤ የ1 ሺህ 500 ሜትር (ቲ11 ቡድን) ሩጫ ውድድርን በ4 ደቂቃ 31 ሰከንድ 77 ማይክሮ ሰከንድ ሪከርድ በመስበርና በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆን ችላለች፡፡
FBC
More Stories
ሩድ ቫንኒስትሮይ ከማንችስተር ዩናይትድ ተሰናበተ
የአለም የማራቶን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው ሩት ቼፕንጌቲች የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ ትሆናለች
ኢትዮጵያና ዑጋንዳ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ