July 2, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024” አውደ ርዕይ በሳይንስ ሙዚዬም ተከፈተ

በሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ላይ ትኩረቱን ያደረገው “ስትራይድ ኢትዮጵያ 2024” አውደ ርዕይ በሳይንስ ሙዚዬም ተከፈተ።በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ዴዔታ ባይሳ በዳዳ(ዶ/ር) ጨምሮ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።በአውደ ርዕዩ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶች እና የቴክኖሎጂ ሥራዎች ለዕይታ ቀርበዋል።ዛሬ በይፋ በሳይንስ ሙዚዬም የተከፈተው አውደ ርዕይ “ሣይንስ በር ይከፍታል ፤ ቴክኖሎጂ ያስተሳስራል ፤ ፈጠራ ወደ ፊት ያራምዳል” በሚል መሪ ሃሳብ እስከ መጪው ግንቦት 18 ቀን እንደሚቆይ ተመላክቷል።

FBC