January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ማንቼስተር ሲቲ የ2023/24 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

ማንቼስተር ሲቲ ብርቱ ፉክክር በታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ሆኗል፡፡በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን ባገኘው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ዌስትሃምን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ 3 ለ1 ማሸነፉን ተከትሎ ነው ሻምፒዮንነቱን ያረጋገጠው፡፡በዚህም 91 ነጥቦችን በመሰብሰብ ፕሪሚየር ሊጉን በበላይነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ለአራት ተከታታይ የውድድር ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማሳካትም ውኃ ሰማያዊዎቹ አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡በሌላ በኩል ሉተን ታዎን፣ በርንሌይ እና ሸፊልድ ዩናይትድ ወደ ሻምፒዮን ሽፕ ወርደዋል፡፡

FBC