የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል፡፡
ጉብኝቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ÷ በግብርና ዘርፍ ያገኘናቸው ስኬቶች በኢንዱስትሪው ዘርፍም በመደገም ላይ ናቸው ብለዋል።
በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የተካሄደውን የመዋቅር እና የአመራር ለውጥ ተከትሎ ተቋሙ ሪቨርስ ኢንጂነሪንግ ዘዴን በመጠቀም የተለያዩ መሳሪያዎችን፣ ሮኬቶችን እና ታንኮችን ለማምረት አስደናቂ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
እያደጉ ያሉ አቅሞች ብልፅግናን ከማረጋገጥ በተጨማሪ ለአህጉራችን ተስፋ እየሆኑ ነውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
አክለውም ፥ በስኬቶቻችን ላይ በመመስረት እና በሰፊ የሰው ኃይላችን በመደገፍ በሁሉም ዘርፎች እና መስኮች እድገታችንን ማፋጠን ይኖርብናል ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።