November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አሜሪካ ከኢራን ጋር በሶስተኛ ወገን በኩል እየተወያየች መሆኗ ተገለጸ

የሁለቱ ሀገራት ውይይት በመካከለኛው ምስራቅ የከፋ ቀውስ እንዳይፈጠር በሚል ነው ተብሏልቀዳሚ ገፅዜናአስተያየትፖለቲካኢኮኖሚማህበራዊልዩልዩስፖርትየመረጃ ሳጥንተመልከትፖለቲካአሜሪካ ከኢራን ጋር በሶስተኛ ወገን በኩል እየተወያየች መሆኗ ተገለጸየሁለቱ ሀገራት ውይይት በመካከለኛው ምስራቅ የከፋ ቀውስ እንዳይፈጠር በሚል ነው ተብሏልአል-ዐይን 2024/5/18 7:13 GMTሀገራቱ በሶስተኛ ወገን በኩል ካሳለፍነው ጥር ጀምሮ በመወያየት ላይ እንደሆኑ ተገልጿልአሜሪካ ከኢራን ጋር በሶስተኛ ወገን በኩል እየተወያየች መሆኗ ተገለጸ፡፡በኢራን ላይ ተደጋጋሚ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን በመጣል የምትታወቀው አሜሪካ በሶስተኛ ወገን በኩል እየተወያየች ነው ተብሏል፡፡አል አረቢያ አክሲስን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳድር ከኢራን ባለስልጣናት ጋር በመወያየት ላይ ነው፡፡አሜሪካ ከኢራን ጋር መወያየትን የመረጠችው በመካከለኛው ምስራቅ እየተከሰቱ ያሉ ቀውሶች እንዳይባባሱ እና ለመቆጣጠር እንዲቻል ነውም ተብሏል፡፡በአሜሪካ በኩል የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መካከለኛው ምስራቅ አማካሪ ብሬት ማክጉርክ እና በኢራን የአሜሪካ አምባሳደር አብራም ፓሌይ ከኢራን ጋር እየተደራደሩ ናቸው የተባለ ሲሆን በኢራን በኩል ግን እስካሁን የተደራዳሪዎቹ ማንነት አልተጠቀሰም፡፡እንዲሁም አሜሪካ እና ኢራን በሶስተኛ ወገን እንዲደራደሩ እያደረገ ያለው አካልም ያልተጠቀሰ ሲሆን ውይይቱ ካሳለፍነው ጥር ወር ጀምሮ በመካሄድ ላይ ተገልጿል፡፡የሁለቱ ሀገራት ውይይት በተለይም የኢራን እና እስራኤል የቀጥታ ግጭት ውስጥ ከገቡበት ሚያዚያ ወር ወዲህ የበለጠ እየተደጋገመ እና እየጠነከረ እንደመጣም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

Al-Ain