July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ፎረም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ፎረም “ከፍተኛ ትምህርት ለላቀ ውጤት” በሚል መሪ ሀሳብ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል።ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ፎረም ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሸኔ፤ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለማሻሻል የተለያዩ ተግባራት እየተከናኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል።ሚኒስትር ዴኤታው፤ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።የጥራት፣ የመልካም አስተዳደር እና የገንዘብ ድጋፍ ችግሮች ተቋማቱን እየፈተ ስለመሆኑ ነው የጠቆሙት።የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለማሻሻል የሪፎርም ስራዎች እየተተገበረ መሆኑን ገልጸው፤የትምህርት ስርዓቱን ለመቀየር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።

EBC