January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቋል፡- የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት

ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናቱ ተጠናቆ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለውሳኔ መላኩን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ገለፀ፡፡የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ቤተልሔም ንጉሴ፤ ኢትዮጵያ የራሷ ኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ስለሌላት በአሁኑ ወቅት ከሉግዘመበርግ ኢ ኤስ ኢ ኩባንያ ኢትዮ ሳትን በመጠቀም ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡ኢትዮ ሳት ኢትዮጵያ ለሳተላይት የምታወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከመቀነስ፣ የባህል ወረራን ከመከላከል እንዲሁም ሀገራዊ እሴትን ከማስጠበቅ አንጻር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ኃላፊዋ አንስተዋል፡፡በኢትዮጵያ ከ2014 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተደራጀው የስፔስ ሳይንስና ጂኢስፓሻል ኢንስቲቲዩ፤ በቀጣይ ኢትዮጵያ የራሷ የኮሙዩኒኬሽን ሳተላይት ባለቤት እንድትሆን የአዋጭነት ጥናት ተጠናቆ ለፕላንና ልማት ሚኒስቴር መላኩንና ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል።

EBC