July 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

በአዘርባጃን በይፋዊ የሥራ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአገሪቱ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሚካይል ጃባሮቭ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።በውይይቱም የሁለቱን አገራት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ተደርሷል።በኢትዮጵያ ያለውን አስተማማኝ የመልማት ጸጋ እና ዕድል ለመጠቀም፣ በተለይም ገቢን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት አዘርባጃን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ሚካይል ጃባሮቭ ገልጸዋል። በኢንቬስትመንትና በስትራቴጂያዊ ስራዎች ያላትን ልምድ ለማካፈልም አገሪቱ ፍላጎት እንዳላት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።በተጨማሪም አገሪቱ በጋራ መልማት የሚያስችሉ ዕድሎችን ሁሉ ለመጠቀም ያላትን ቁርጠኝነት ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

EBC