November 23, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በክልሉ ከ6700 በላይ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፍቃድ ምዘና ሊካሄድ ነው።

በክልሉ ከ6700 በላይ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፍቃድ ምዘና ሊካሄድ ነው።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመምህራን የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፍቃድ ምዘና ሊካሄድ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታዉቋል።የሙያ ፍቃድ ምዘና ግንቦት 24/2016 ዓ/ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮዉ ገልጿል። የሙያ ፍቃድ ምዘናዉበቦንጋ ፣በሚዛን አማን፣በታርጫ ፣በቴፒ ፣በአመያ እና ጀሙ የሚሰጥ ሲሆን በካፋ፣ በዳውሮ እና በሸካ ዞኖች ተጨማሪ የምዘና ማዕከላትን ከዞኖቹ ጋር በመነጋገር ለመስጠት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።ምዘናዉ በዲፕሎማ ተመርቀዉ በማስተማር ላይ የሚገኙ ተመዛኞች ፦ አማርኛ-1741፣ እንግሊዝኛ-1988 ፣ ሒሳብ -668 ፣ሒሳብና አከባቢ ሳይንስ-1768 ፣ሒሳብና ተፈጥሮ ሳይንስ-506 ፣የትምህርት ቤት አመራሮች -107 በጠቅላላ 6778 መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሚመዘኑ መሆናቸዉን የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የክልሉ ትምህርት ቢሮን ጠቅሶ ዘግቧል።

You may have missed