January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ እንድታመርት ብቻ ሳይሆን ያመረተችውን እንድትጠቀም መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል፡- ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

ኢትዮጵያ እንድታመርት ብቻ ሳይሆን ያመረተችውን እንድትጠቀም መንግስት ትልቅ ትኩረት መስጠቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህልን እንዲያጎለብት ጥሪ አቅርበዋል።ትላንት ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመናል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

EBC