November 22, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ግብጽ እስራኤል በዓለም አቀፉ የጦር ፍርድ ቤት እንድትጠየቅ የተጀመረውን ጥረት ተቀላቀለች

ግብጽ እስራኤል በዓለም አቀፉ የጦር ፍርድ ቤት እንድትጠየቅ የተጀመረውን ጥረት ተቀላቀለች፡፡

ለፍልስጤም ነጻነት እታገላለሁ የሚለው ሐማስ ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነበር ጦርነት የተቀሰቀሰው።

እስራኤል በሐማስ ታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ነው ጥቃት ባለችው የመልሶ ማጥቃት ከ34 ሺህ በላይ ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል።

በእስራኤል በኩል ደግሞ 1 ሺህ 200 ዜጎች መገደላቸውን ተከትሎ የእስራኤል ጦር በጋዛ የተለያዩ ቦታዎች ላይ የምድር እና አየር ላይ ጥቃቶችን እያደረሰ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ ለፍልስጠየማዊያን የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ሚገባበት እና በግብጽ ድንበር አቅራቢያ ባለው ራፋህ መጠለያ አዲስ ጥቃት መጀመሯን ተከትሎ አሜሪካንን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እያወገዙ ናቸው፡፡

አሜሪካ እስራኤል በራፋህ ድንበር ላይ እያደረሰችው ያለውን ጥቃት እንድታቆም የተለያዩ ጨናዎችን በማድረስ ላይ ሲሆን ለአብነትም የቦምብ ድጋፍ እንዳይደረግ እገዳ ሲጥል ካናዳ እና ሌሎችም ሀገራት ለእስራኤል የጦር መሳሪያ እንዳይሸጥ ከልክለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት እስራኤል በራፋህ የጀመረችውን ጥቃት እንዲያስቆም ጠይቀዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ የአለማቀፉ ፍርድቤት እስራኤል ከራፋህ እንድትወጣ እንዲያዝ ጠየቀች

አሁን ደግሞ ግብጽ በደቡብ አፍሪካ የቀረበውን ጥያቄ መቀላቀሏን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሳሜህ ሽኩሪ በኩል ማስታወቋን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ከግብጽ እና ደቡብ አፍሪካ በተጨማሪም ቱርክ እና ኮሎምቢያ በይፋ እስራኤል በዓለም አቀፉ ጦር ወንጀል ፍርድ ቤት እንድትጠየቅ በይፋ ግፊት እያደረጉ ካሉ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ሆነዋል፡፡

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው ሀገራቸው በዓለም አቀፉ የጦር ፍርድ ቤት እንዲጠየቁ ያቀረቡ ሀገራትን የተቹ ሲሆን በተለይም በቅርቡ የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንትን አስተያየት ውድቅ አድርገዋል፡፡

Al-Ain

You may have missed