July 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአሳማ ኩላሊት ተገጥሞለት የነበረው አሜሪካዊ ህይወቱ አለፈ

  • በአሜሪካ 100 ሺህ ዜጎች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና ወረፋ በመጠበቅ ላይ ናቸውየአሳማ ኩላሊት ተገጥሞለት የነበረው አሜሪካዊ ህይወቱ አለፈ፡፡የ62 ዓመቱ ሪክ ሰላይማን አሜሪካዊ ሲሆን ከ11 ዓመት በፊት ነበር የኩላሊት መድከም አጋጥሞት ወደ ማሳቹሴትስ ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል ያመራው፡፡ከበጎ ፈቃደኛ በተገኘ ኩላሊት ንቅለ ተከላ በ2018 የተደረገለት ይህ አሜሪካዊ በድጋሚ ኩላሊቱ ስራ ማቆሙን ተከትሎ በቤተ ሙከራ የለማ የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ተሰርቶለት ነበር፡፡ከሁለት ወራት በፊት የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላውን አጠናቆ ወደ መኖሪያ ቤቱ አምርቶ ሲኖር የነበረው ይህ ሰው አሁን ላይ ህይወቱ እንዳለፈ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡ንቅለ ተከላውን ያደረገው የማሳቹሴትስ ዩንቨርሲቲ በሪክ ሞት ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ግለሰቡ በቤተ ሙከራ የለማው የአሳማ ኩላሊት እንዲገጠምለት ፈቃደኛ የሆነው ምርምሩ ተሳክቶ ሌሎች ታማሚዎች እንዲጠቀሙ በሚል ነበር ብሏል፡፡በኢትዮጵያ 4 ሺህ 800 የኩላሊት እጥበት እያደረጉ ከሞት ጋር የሚታገሉ ህሙማን መኖራቸው ተገለጸሆስፒታሉ አክሎም ለሪክ በተደረገው የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ በርካታ ትምህርቶች እንደተገኙ ሙከራው በቀጣይ የበለጠ ስኬታማ እንዲሆን ያስችላልም ብሏል፡፡ይሁንና የአሳማ ኩላሊት የተገጠመለት ሪክ በድንገት ህይወቱ ያለፈው ለምን እንደሆነ፣ ከንቅለ ተከላው ጋር የተያያዘ ይሁን አይሁን ምርመራ በመደረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡የሪክ ቤተሰቦች በበኩላቸው ልጃቸው የመዳን ተስፋ እንደነበረው እና ለመኖር እንደጓጓ ህይወቱ ማለፉን ተናግረዋል፡፡በአሜሪካ 100 ሺህ ሰዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና እንዲደረግላቸው ወረፋ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ የሀገሪቱ ጤና ጥበቃ ጥናት ያስረዳል፡፡በቤተ ሙከራ የለማ የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ እየጠበቁ ያሉ አሜሪካዊያንን የገጠማቸውን የኩላሊት እጥረት እንደሚፈታ ታምኖበታል፡፡
  • Al-Ain