January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የተጣበቁ መንታ ህፃናት ተወለዱ

በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የተጣበቁ መንታ ህፃናት ተወለዱበአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የፅንስና ማህፀን ስፔሻሊስት ዶክተር አረጋኸኝ ሙሉጌታ ህፃናቱ ሁለት ጭንቅላት፣ አራት እጅ፣ አራት እግር ያላቸው ሲሆን የጋራ የሆነ አንድ ልብና አንድ እትብት እንዳላቸው አስረድተው ሁለቱም ጾታቸው ወንድ መሆኑን ተናግረዋል።ለምርመራ ወደ ሆስፒታሉ ከመጡበት 8ኛ ወር ጀምሮ ክትትል ሲደረግላቸው የቆዩት እናት በቀዶ ጥገና በሠላም መገላገላቸው ተገልጿል።እንደዚህ አይነት ክስተቶች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ መሆናቸውን ገልፀው እናቶች የእርግዝና ምርመራ በወቅቱና በአግባቡ ቢያደርጉ ችግሩ ሊፈታ የሚችልበትም አጋጣሚ አለ ብለዋል፡፡ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ሰአትህጻናቱ እና እናታቸው በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡

SRTA