
ሃማስ ወታደራዊ ክንፍ ከወደ ራፋህ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙም ተገልጿል 300 ሺህ የሚጠጉ ፍልስጤማውያን ከምስራቃዊ ራፋህ መውጣታቸውን የእስራኤል ጦር አስታወቀ።ጦሩ በዛሬው እለት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ፥ ፍልስጤማውያኑ ወደ “አል ማዋሲ” እና ሌሎች ጊዜያዊ ማረፊያዎች እያቀኑ መሆኑን ጠቁሟል።ከሰኞ ጀምሮ ፍልስጤማውያን ከራፋህ እንዲወጡ የሚጠይቁ ጽሁፎችን ከአውሮፕላኖች ላይ የበተነችው እስራኤል፥ ከራፋህ ባሻገር ንጹሃን የሃማስ ታጣቂዎች መሽገውባቸዋል ካለቻቸው የጃባሊያ የስደተኞች ጣቢያ እና ከሌሎች 11 አካባቢዎች እንዲወጡም አሳስባለች።
Al-Ain
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ንግግር ለመጀመር አጥጋቢ እቅድ እንዳልደረሳት ገለጸች