ለ #ጽዱኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 50 ሚሊየን ብር ለማሳባሰብ ያለመ የዲጂታል ቴሌቶን በዛሬው ዕለት ይካሄዳል፡፡መላው ኢትዮጵያውያንም በዚህ ዕድል ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ በክብር ተጋብዘዋል፡፡የቴሌቶኑ ተሳታፊዎችም በሚመቻቸው አማራጭ ቀጥለው በተቀመጡት የባንክ ሒሳብ ቁጥሮች ገንዘቡን ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 በስዊፍት ኮድ NBETETAA በዲጂታል ባንኪንግ ከንግድ ባንክ ወደ ንግድ ባንክ በአንድ ጊዜ 100,000 ብር በቀን 6 ጊዜ መላክ ይቻላል ከሌላ ባንክ ወደ ንግድ ባንክ ሲላክ ደግሞ በአንድ ጊዜ 25,000 ብር በቀን 4 ጊዜ መላክ ይቻላልየሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።የንቅናቄውን ይፋ መሆን ተከትሎም በርካታ ተቋማት፣ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ ባለሃብቶች እንዲሁም የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች አቅማቸው የፈቀደውን አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡በዛሬው ዕለትም ለ#ጽዱኢትዮጵያ በአንድ ጀንበር 50 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ ባለመው ንቅናቄ መላው ሀገር ወዳድ ሁሉ በንቃት እንዲሳተፍ ተጋብዟል፡፡
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።