
ኳታር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ እንደሚፈልጉ ተገለጸ፡፡በኳታር፣ የመን እና ኢራን የኢፌዲሪ አምባሳደር ፈይሰል አልይ ከኳታር የኢንቨስትመንት ባለስልጣን የአፍሪካ ዳይሬክተር ሱልታንአል ሳዓዲ እና ልዑካቸው ጋር ተወያይተዋል፡፡አምባሳደር ፈይሰል÷ በኢትዮጵያ በሆቴል ቱሪዝም፣ በታዳሽ ኃይልና በአምራች ኢንዱስትሪ የኢንቨስትመንት ዘርፍ የውጭ ኩባንያዎች እንዲሰማሩ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠራቸውን አስረድተዋል፡፡የኳታር ኢንቨስትመንት ባለስልጣን የሀገሪቱ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግም ጠይቀዋል፡፡ ሱልታንአል ሳዓዲ በበኩላቸው÷ የኳታር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።