November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የፊታችን እሑድ ለጽዱ ኢትዮጵያ 50ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር ለማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን ይካሄዳል

የፊታችን እሑድ ግንቦት 4 ለ#ጽዱኢትዮጵያ 50ሚሊየን ብር በአንድ ጀምበር የዲጂታል ቴሌቶን ላይ ዜጎች እንዲሳተፉ እድል መሰናዳቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡

በጋራ ትርጉም ያለው በጎ ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት፤ ኢትዮጵያውያን የፊታችን ግንቦት 4 የሚከናወነውን የ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በመገንባት ክብርን ጠብቆ የመፀዳዳት ባህልን ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዝያ 18 ቀን 2026 ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በርካቶች በመቀላቀል ድጋፍ እያደረጉ ይገኛል።

በዚህ ንቅናቄ እስካሁን ድርስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶች፣ የተለያዩ ተቋማት እንዲሁም በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚኖሩ ዜጎች አቅማቸው የፈቀደውን ገንዘብ በመደገፍ ለዓላማው መሳካት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

በርካቶች እየተቀላቀሉት ያለውን ይህን ንቅናቄ ዜጎች እንዲሳተፉ ለማድረግም የፊታችን እሑድ ግንቦት 4 በአንድ ጀምበር 50 ሚሊዮን ብር ዲጂታል ቴሌቶን መሰናዳቱ ተገልጿል፡፡

በንቅናቄው በመሳተፍ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ዜጎች በንግድ ባንክ አካውንት 1000623230248 እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ ዶላር አካውንት 0101211300016 “ጽዱ ኢትዮጵያ” ማበርከት እንደሚችሉም ተጠቁሟል።

EBC