የኢትዮጵያና የአሜሪካን 120ኛ ዓመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያወሳ “120 ዓመታት የሁለትዮሽ ምስላዊ ጉዞ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ምስላዊ ዓውደ ርዕይ በይፋ ተከፍቷል።
በሁነቱ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ፥ ሁለቱ ሀገራት በትምህርት፣ በጤና፣ በኢኮኖሚ ለ120 ዓመታት የነበራቸውን ትብብር ወደፊትም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የሀገራቱን የረጅም ዓመታት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ዓውደ ርዕዩ አጋዥ ምህዳር የሚፈጥር ነው ያሉት ደግሞ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ናቸው።
ዓውደ ርዕዩ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም ከሚያዝያ 30 እስከ ግንቦት 18፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ከግንቦት 21 እስከ ሰኔ 1 እንዲሁም በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል ከሰኔ 10 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል ተብሏል፡፡
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።