
ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከቤንዚን ውጪ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።በዓለም ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መነሻ በማድረግ በቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ብቻ መጠነኛ ማሻሻያ መደረጉን ሚኒስቴሩ አመልክቷል።በመሆኑም ከግንቦት 1 ቀን 2016 ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የአይሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።በዚህም መሰረት:-
ቤንዚን ……………………………………… ብር 78.67 በሊትር
ነጭ ናፍጣ………………………………… ብር 79.75 በሊትር
ኬሮሲን …………………………………… ብር 79.75 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ………………… ብር 70.83 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ…………………… ብር 62.36 በሊትርከባድ
ጥቁር ናፍጣ…………………. ብር 61.16 በሊትር ሆኗል።
More Stories
ትራምፕ በብረት እና አልሙኒየም ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ ጣሉ
ከውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደር እየተዘጋጁ መሆኑን ባንኮች ገለጹ
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ