November 24, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአፍሪካ የአፈር ማዳበሪያ ምርትን ለማሳደግ 15 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

 በአፍሪካ የአፈር ማዳበሪያ ምርትን ለማሳደግ 15 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ገለፀ፡፡

ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የአፈር ማዳበሪያ እና የአፈር ጤና ጉባኤ ላይ÷ በአፈር ማዳበሪያ ፖሊሲ፣ ጥናት እና ልማት ዙሪያ የአፍሪካ ሀገራት በትብብር ሊስሩ እንደሚገባ ህብረቱ አስገንዝቧል።

በአፍሪካ የአፈር ማዳበሪያ ምርትን ለማሳደግ 15 ቢሊዮን ዶላር የግሉ ሴክተር ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልግ ገልጾ÷ ይህም የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር አመልክቷል።

ለዚህም የአፍሪካ ሀገራት የግል ሴክተሩን የገበያ ትስስር በመፍጠር እና የስራ ካፒታል ድጋፍ በማድረግ ሊያበረታቱ እንደሚገባም ጠቁሟል፡፡

ህብረቱ በ2033 በአህጉሪቱ የሚመረተውን የአፈር ማዳበሪያ መጠን በሶስት እጥፍ ለማሳደግ እቅድ መያዙን አስታውቋል፡፡

የግሉ ሴክተር የኢንቨስትመንት ድጋፍ ካደረገ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት እና ማዕድናት ያላት አፍሪካ የአፈር ማዳበሪያን በቀላሉ በማምረት የግብርና ምርቷን ማሳደግ እንደምትችል መገለፁን ኔይራ ሜትሪክስ ዘግቧል፡፡

FBC

You may have missed