
በሕንድ በጫካ ውስጥ የሚኖሩ የአንድን መነኩሴ የመምረጥ መብት ለማረጋገጥ ሲባል ለብቻቸው የምርጫ ጣቢያ ተቋቁሞላቸዋል።
969 ሚሊዮን ዜጎች ድምጽ ለመስጠት የተዘጋጁበት የህንድ ምርጫ እየተካሄደ ሲሆን፤ በዓለማችን ለብዙ ቀናት የሚከናወን ግዙፉና ውዱ ምርጫም ነው።
በሀገረ ህንድ የአንድን መነኩሴ ዴሞክራሲያዊ የመምረጥ መብት ለማረጋገጥ የተሄደበት ርቀት አንድ ድምጽ ያለው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ የሚያሳይም ነው ተብሏል፡፡
የምርጫ ሕጎች እያንዳንዱ መራጭ ከድምጽ መስጫ ጣቢያው ከ2 ኪሎ ሜትር በላይ እንዳይርቅ ይጠይቃሉ።
በጉጅራት ግዛት ጅር ጥብቅ ደን ውስጥ ለሚኖሩ አንድ የሂንዱ መነኩሴ የመምረጥ ዕድል ለመስጠት ፤ የምርጫ አስፈፃሚ ባለሙዎች ረጅም እና አስቸጋሪ በሆነ መንገድ በአውቶቡስ የሚደረግ ጉዞን ጨምሮ የሁለት ቀናት ጉዞ አድርገዋል።
የጅር ጫካ በህንድ በጣም አደገኛ የኢዤያ አንበሶች የሚኖሩበትና ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ደኖች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
EBC
More Stories
ሩሲያ በዩክሬን የኢነርጂ መሰረተ ልማት ተቋማት ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት ለማቆም ተስማማች
አሜሪካ በየመን የሀውቲ ታጣቂዎች ላይ አዲስ የአየር ጥቃት መፈጸሟ ተገለጸ
ትራምፕ “የወንበዴ” ቡድን አባላት ናቸው ያሏቸውን ከ200 በላይ ቬንዙዌላውያን ከአሜሪካ አባረሩ