
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦሮሞ ሕዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅና አንድነቱን ማጽናት እንዳለበት አስገነዘቡ፡፡
ከአራቱም የወለጋ ዞኖች የተውጣጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሀገራዊ ለውጡን የሚደግፍ ሰልፍ በነቀምቴ ከተማ ወለጋ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝባዊ የድጋፍ መድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሠላም፣ አንድነትና የኢኮኖሚ ነጻነትን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ሐሳቦችን አንስተዋል::
የኦሮሞ ሕዝብ ያገኘውን ለውጥ በማስቀጠል ሠላሙን መጠበቅና አንድነቱን ማጽናት እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
በአካባቢው የተገኘውን ሠላም ኅብረተሠቡ ማስቀጠል እንደሚኖርበት ማስገንዘባቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
FBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ