July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከፊታችን ግንቦት የፓሪስ ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ሰነ-ስርዓት በቦንጋ ከተማ እንደሚካሄድ የደ/ም/ኢ/ህ/ክ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከፊታችን ግንቦት 2-3/2016 ዓመተ ምህረት የፓሪስ ኦሎምፒክ ችቦ የማብራት ሰነ-ስርዓት በቦንጋ ከተማ እንደሚካሄድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአደባባይ የችቦ ማብራት ስነ-ስርዓት ከተካሄደ በኋላ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልል ርክክብ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

የቢሮው  ሀላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ የፓሪስ ኦሎምፒክ የችቦ ማብራት ስነ-ስርዓት ለማካሄድ የሚያስችሉ ተግባራትን የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመው እያከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ግንቦት 2/2016 ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የስፖርት ቤተሰቦች የሚሳተፉበት የፓናል ውይይት ይደረጋል፡፡

በመቀጠልም ግንቦት 3/2016 ዓ.ም መላው ማህበረሰብ የሚሳተፍበትና የክልላችንን ገጽታ የምናስተዋውቅበት እንግዳ አቀባባል በአደባባይ ችቦ የማብራት ስነ-ስርዓት ተካሄዶ ለሲዳማ ብሄራዊ ክልል መንግስት የማስረከብ ስራ እንደሚከናወን አቶ  ፋንታሁ ገልጸዋል፡፡

በዕለቱ ሩጫን ጨምሮ የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች የሚካሄዱ ሲሆን ህብረተሰቡ በመርሃ ግብሩ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

መረሃ ግብሩ  በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስተባባሪነት እንደሚሰራና የፌዴራል፣ የክልልና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚሳተፉም ተገልጿል፡፡

የኦሎምፒክ ችቦ ዓለም ሀገራትን የሚዞርበት ዋና ዓላማ  ወንድማማችነት፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነትንና አብሮነትን ለማጠናከር እንዲሁም የአንድ  አካባቢን  ባህልና ወግ ለማስተዋወቅ  ታሶቦ እንደሆነ  የአለም አቀፉ  ኦሎምፒክ ኮሚቴ  መርህ ያሣያል ፡፡

ዘጋቢ ፡ ብዙአየሁ ጫካ-ከቦንጋ