ሩሲያ ከሴራሊዮን ጋር በኒውኩሌር ኃይል ዙሪያ በትብብር ለመስራት ማሰቧን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ገልጸዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት ከሴራሊዮን አቻቸው ቲሞቲ ሙሳ ካባ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።
ኒውኩሌር ኃይል እና ሰላማዊ አቶሚክ ኢንዱስትሪን ጨምሮ የሩሲያ ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ሙዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ የሴራሊዮን መንግስት በሚያቀርበው ጥያቄዎች ላይ መስማማታቸው ተገልጿል።
ሞስኮ በፈረንጆቹ 2024 መጨረሻ ላይ በሴራሊዮን ኤምባሲዋን ለመክፈት ማቀዷንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ ተናግረዋል፡፡
ላቭሮቭ በሞስኮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሩሲያ ኤምባሲዋን በፍሪታውን ለመክፈት እንደወሰነችና በጉዳዩ ላይም ሀገራቱ እየሰሩበት እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
አክለውም ሀገራቱ በሴራሊን መሠረተ ልማት መገንባትን ጨምሮ በኒውኩሌር ኃይል ዙሪያ በትብብር ለመስራት ማሰባቸውን መናገራቸውን አርቲ ዘግቧል፡፡
FBC
More Stories
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር
እስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች