
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታክቲካል (ስልታዊ) የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ እንዲደረግ ለሀገሪቱ ጦር ትዕዛዝ መስጠታቸው ተሰምቷል፡፡ልምምዱ አንዳንድ ምዕራባውያን ባለስልጣናት የሚሰነዘሩትን ጠብ አጫሪ መግለጫ እና ዛቻ ተከትሎ የሚካሄድ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ትዕዛዙን ተከትሎ ሩሲያ ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎቿን የማድረግ አቅም በቅርቡ መፈተሽ ትጀምራለች፡፡በልምምዱ የደቡብ ወታደራዊ ዲስትሪክት ሚሳኤል ሃይሎች፣ ወታደራዊ አውሮፕላኖች እና የሩሲያ የባህር ኃይል እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡ልምምዱ ስልታዊ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን አቅም ለመፈተሽ እና በተመረጡ ቦታዎች ለማሰማራት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ፕሬዚዳንት ፑቲን÷ ሩሲያ የግዛት አንደነቷንና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የሀገሪቱ ጦር በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውንም አር ቲ ዘግቧል፡፡
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።