
ስፔናዊው አሰልጣኝ ጁለን ሎፔቴጉይ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማምተዋል፡፡ስምምነቱ ተፈጻሚ ከሆነም የ57 ዓመቱ የቀድሞ የዎልቭስ አሰልጣኝ በድጋሚ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡የመዶሻዎቹ አለቃ ዴቪድ ሞይስ ዌስትሃም ባለፉት 9 ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ብቻ ማሸንፉ እና ከዩሮፓ ሊግ ውጪ መሆኑን ተከትሎ ጫና ውስጥ ገብተው ቆይተዋል፡፡በዚህ ክረምት የኮንትራት ውላቸው የሚጠናቀቀው ዴቪድ ሞይስ የክለብ ቆይታቸውን በተመለከተ የፊታችን ግንቦት 19 ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በኋላ ንግግር እንደሚጀመሩ ገልጸው ነበር፡፡ይሁን እንጂ ትላንት ምሽት በቼልሲ የ5 ለ 0 ሽንፈት ያጋጠማቸው አሰልጣኙ÷ ጁለን ሎፔቴጉይ ከዌስትሃም ጋር የሚፈራረሙ ከሆነ ከመዶሻዎቹ አሰልጣኝነት በይፋ የሚሰናበቱ ይሆናል፡፡የቀድሞ የስፔን እና የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ የነበሩት ጁለን ሎፔቴጉይ ከወልቭስ አሰልጣኝነት ከተሰናበቱ በኋላ ድጋሚ ወደ እንግሊዝ ለመመለስ ፍላጎት እንደነበራቸው ሲገልጹ መቆየታቸውን ቢቢሲ ስፖርት አስነብበቧል፡፡
FBC
More Stories
ኢትዮጵያ በፊፋ ደረጃ 147ኛ ሆናለች
ኬቨን ዲብሮይን በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ማንቼስተር ሲቲን እንደሚለቅ ተረጋገጠ
በማሻ ወረዳ በህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ለተከታታይ 5ቀን ስካሄድ የነበረው የእግርኳስ ውድድር ፍጻሜውን አግኝተዋል።