January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የእስራኤል ካቢኔ በአገሪቱ የሚገኘውን የአልጀዚራ ቢሮ ለመዝጋት ውሳኔ ላይ መድረሱ ተገለጸ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ናታኒያሁ ዛሬ በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ባጋሩት መረጃ፥ ካቢኔያቸው በእስራኤል የሚገኘውን የአልጀዚራ ቢሮ ለመዝጋት ከውሳኔ ላይ መድረሱን ገልጸዋል። እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ፥ ውሳኔው በአልጀዚራ ላይ ስለሚኖረው ተፅዕኖ እና መቼ ተግባራዊ እንደሚደረግ ግን የተባለ ነገር የለም፤ ውሳኔው ዘላቂ ይሁን ጊዜያዊም የታወቀ ነገር የለም።ውሳኔው በእስራኤል እና በአልጀዚራ መካከል የቆየውን ቁርሾ እንደሚያባብሰው ይጠበቃል።የአልጀዚራ ቻናል ባለቤት የሆነችው ኳታር የጋዛን ጦርነት ለማስቆም እየተደረገ ባለው ጥረት ቁልፍ ሚና እየተጫወተች መሆኑ ይታወቃል።በመሆኑም በዚህ ሰዓት የተላለፈው የእስራኤል ካቢኔ ውሳኔ በሁለቱ አገረት መካከል ውጥረት እንዳያነግስ ተሰግቷል። እስራኤል እርሷን በተመለከተ የተዛቡ ዘገባዎችን ያሰራጫል የምትለውን አልጀዚራን ከሀማስ ጋር በማበር ጭምር ትከሰዋለች። አልጀዚራ በጦርነቱ ወቅት ጋዛን ለቀው ካልወጡ ጥቂት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አንዱ ነው።ቻናሉ አሰቃቂ የአየር ጥቃት እና የሆስፒታል ትዕይንቶችን ከጋዛ በቀጥታ ሲዘግብ እና እስራኤልን በጅምላ ጭፍጨፋ ሲከስ ቆይቷል።

EBC