November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ከሚያስመዘግቡ የዓለም ሀገራት ውስጥ አንዷ ሆነች

On May 6, 202ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2024 እስከ 2029 ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ከሚያስመዘግቡ የዓለም ሀገራት ውስጥ አንዷ እንደሆነች ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ገለጸ፡፡በዓለም ሀገራት ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን የሚያስተዋውቀው ቪዥዋል ካፒታሊስት የመረጃ ምንጭ አይ ኤም ኤፍን መረጃ ጠቅሶ ከፈረንጆቹ 2024 ጀምሮ እስከ 2029 ፈጣን የገብያ ትስስር ያላቸውን ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡በዚህ ዝርዝር ውስጥ ጋያና፣ ሞዛምቢክ፣ ሩዋንዳ እና ባንግላዲሽ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ ኢትዮጵያ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ኒጀር፣ ኡጋንዳ፣ ሕንድ፣ ቬተናም እና ሴኔጋል ደግሞ በቅደም ተከትል እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ የያዙ ሀገራት ናቸው፡፡የተጠቀሱት ሀገራት ካላቸው እምቅ የተፈጥሮ ሃብት አንፃር በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከዓለም አማካይ ኢኮኖሚ በእጥፍ ያድጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡የሀገራት ከፍተኛ የገብያ ትስስር መፍጠር ኢኮኖሚያቸውን ከማሳደግ በተጨማሪ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢንቨስትሮችን ትኩረት ለመሳብ የስነ ህዝብ ለውጥ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

FBC