January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዡዩአን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች አመራሮችም ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገውላቸዋል፡፡በኢትዮጵያ የነበራቸው የሥራ ጊዜ ስኬታማ እንደነበር የገለጹት አምባሳደር ዣኦ ዡዩአን÷በሁለቱ ሀገራት ያለው ትብብር 50 ዓመታትን ከመሻገሩ ባለፈ ወደ ስትራቴጂያዊ አጋራነት ማደጉን ጠቅሰዋል።አምባሳደሩ በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ያደረጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡በሥራ ቆይታቸው በቻይና መንግስት ድጋፍ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የነበሩ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ለፍጻሜ መብቃታቸው ተጠቁሟል፡፡ኢትዮጵያ ብሪክስን እንድትቀላቀል ቻይና ያደረገችው ድጋፍ የሁለቱ ሀገራት የረዥም ዘመን ጠንካራ ወዳጅነት ሌላኛው ማሳያ መሆኑም ተወስቷል።

FBC