በአዲስ አበባ የትንሳኤ በዓል ምንም ዓይነት አደጋ ሳይከሰት በሰላም ተከብሮ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።ሕብረተሰቡ የቅድመ ጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላሳየው ትብብርም ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል።የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ በዋዜማው በተከሰተ የእሳት አደጋ ሕይወቱ ካለፈ አንድ ግለሰብ ውጪ ሌላ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አለመድረሱን ገልጸዋል።ቅዳሜ ምሽት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ጄነሬተር ለማስነሳት ነዳጅ በመጨመር ላይ የነበረ የ26 ዓመት የሆቴል ሰራተኛ በጄነሬተሩ ላይ በተነሳ እሳት ወዲያው ሕይወቱ ማለፉን አመልክተዋል።በበዓል ወቅት ሊኖር ከሚችለው የአደጋ ተጋላጭነትና ስፋት አኳያ አደጋዎች አለመከሰታቸውን ጠቅሰዋል።ኮሚሽኑ ከበዓሉ አስቀድሞ ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በስፋት ማከናወኑን አስታውሰዋል።ማህበረሰቡ የቅድመ አደጋ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ መተግበሩ በዓሉ በሰላም እንዲያልፍ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰው ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
EBC
More Stories
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል