
የአሜሪካ አየር ሀይል በሶሪያ ቁልፍ የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል የተገደለው ሰው በመጨረሻም ዶሮ አርቢ ሆኖ መገኘቱን አረጋግጫለሁ ብላለች
የአሜሪካ አየር ሀይል በሶሪያ ቁልፍ የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል የተገደለው ሰው በመጨረሻም ዶሮ አርቢ ሆኖ መገኘቱን አረጋግጫለሁ ብላለች
የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል በስህተት በአሜሪካ ጦር የተገደለው ሰው የ60 ዓመት ሶሪያዊ አርሶ አደር ነበር
አሜሪካ የአልቃይዳ መሪ ነው በሚል ገድየዋለሁ ያለችው ድሃ ገበሬ ሆኖ ተገኘ፡፡
የአሜሪካ አየር ሀይል ጦር በሶሪያ የሚንቀሳቀሰው አልቃይዳ ቁልፍ አመራር ነው በሚል ነበር የድሮን ጥቃት የፈጸመው፡፡
ጥቃቱም ውጤታማ እንደነበር እና የአልቃይዳ አመራር መገደሉንም ሀገሪቱ አስታውቆም ነበር፡፡
ባሳለፍነው ግንቦት ወር ላይ እንደተፈጸመ የተገለጸው ይህ ጥቃት ኢላማውን እንደሳተ እና በዶሮ እርባታ የሚተዳደር አርሶ አደር ስለመገደሉ በወቅቱ የሟች ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡
ይህ ጥቆማ የደረሰው የአሜሪካ አማዕከላዊ እዝም ባደረገው ማጣራት በወቅቱ በተፈጸመው ጥቃት የተባለው የአልቃይዳ መሪ ሳይሆን ሉፍቲ ሀሰን ማስቶ የተሰኘ ዶሮ አርቢ አርሶ አደር እንደተገደለ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ይፋ ባደረገው ምርመራ የ60 ዓመቱ አዛውንት በተፈጸመው የድሮን ጥቃት እንደተገደለ ይህም ስህተት መሆኑን አረጋግጠናልም ብሏል፡፡
በአሜሪካ የሰው አልባ አውሮፕላን ወይም ድሮን ጥቃት በስህተት የተገደለው ማስቶ ወንድም በበኩሉ ወንድሙ ዶሮ ከማርባት እና በግ ከመንዳት ውጪ ከአልቃይዳም ሆነ ከየትኛውም ቡድን ጋር ግንኙነት የሌለው ሰው ነው ብሏል፡፡
Al-Ain
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ