
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መጪውን የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ለሚኖሩ አቅመ ደካሞችና በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ።
ፕሬዚዳንቷ በዚህ ወቅት በስተላለፉት መልዕክት÷ ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ መደጋገፍ የእለት ተእለት ተግባር መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
መጪውን የትንሳኤ በዓል ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር አብሮ ማሳለፍ ይገባል ማለታቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክፍሉ ገዛኸኝ÷ ፕሬዚዳንቷ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበው መንግስት ለነዋሪዎች ተጠቃሚነት የተለያዩ ድጋፎች እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው ነዋሪዎች ፕሬዚዳንቷ የትንሳኤ በዓልን ተደስተው እንዲውሉ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነዋል።
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።